ባህር ዳር ከነማ ፋሲል ተካልኝን አሰልጣኝ አድርጎ ሊሾም ነው

ባህር ዳር ከነማ የቅ/ጊዮርጊሱን ም/አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝን የአሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው (ማንጎ) ተተኪ አድርጎ ሊሾም ተቃርቧል ።

የጣና ሞገዶችን ለመጀመሪያ ጊዜ ከከፍተኛ ሊግ ወደ ኘሪምየር ሊግ ያሳደጉት አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው (ማንጎ) የኮንትራት ውላቸው ተጠናቆ ከባህርዳር ከነማ ጋር መለያየታቸውን ተከትሎ ቡድኑን ማን ይረከባል የሚለው የበርካቶች ጥያቄ ሆኖ የቆየ ሲሆን አማራ ስፖርት ከክለቡ ባገኘነው መረጃ መሰረት አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ሞገዶችን ሊረከብ መቃረቡን ገልፀውልናል ።

አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ በብርቱካናማው መለያ በፈረሰኞቹ ቤት በተጫዎችነት እና በም/አሰልጣኝነት በርካታ ስኬታማ አመታትን ያሳለፈ ሲሆን ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንም መጫዎት ችሏል ።

አሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ በኢንስትራክተር አብራሃም መብራህቱ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ም/አሰልጣኝም መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በቅርቡ ወደ ስፔን እና ሀንጋሪ በማቅናት የሙያ አጋሩ ከሆነው እድሉ ደረጀ ጋር የእግርኳስ ስልጠናዎችን ተከታትሎ ተመልሷል ።

ባህርዳር ከነማዎች በ2012 የውድድር ዘመን የዋንጫ ተፎካካሪ ለመሆን የፊታችን ሀሙስ ሐምሌ 25 በሚከፈተው የተጨዋቾች የዝውውር ገበያ ላይ በሰፊው እንደሚሳተፉ ይጠበቃል ።

©www.AmharaSport.net

error: እባክዎትን ኮፒ ሲያደርጉ ምንጭ ይጥቀሱ!