ቅ/ጊዮርጊስ ሁለት የደደቢት አማካዮችን አስፈረመ

ቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለት የደደቢት አማካዮችን አቤል እንዳለና የአብስራ ተስፋዬን በማስፈረም ወደ ተጨዋቾች የዝውውር ገበያ ገብቷል ።

ቅ/ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በይፋዊ ገፁ በደደቢት እግርኳስ ክለብ በግላቸው ጥሩ የውድድር ዓመታት ያሳለፉትን ሁለት ተስፈኛ የአማካይ ስፍራ ተጨዋቾች አቤል እንዳለና የአብስራ ተስፋዬን ዛሬ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል ።

ሁለቱም ተጫዋቾች ፊርማቸውን ካኖሩ በኋላ ከክለቡ የሚዲያ ዝግጅት ክፍል ጋር በነበራቸው ቆይታ ፈረሠኞቹን በመቀላቀላቸው ልዩ ስሜት እንደፈጠረባቸውና ኩራት እንደተሰማቸው መናገራቸውን መረጃውን ከክለቡ ይፋዊ ገፅ አግኝተናል ፡፡

www.AmharaSport.net

error: እባክዎትን ኮፒ ሲያደርጉ ምንጭ ይጥቀሱ!