አሰልጣኝ አስራት አባተ ቡታጅራ ከተማን ተረክቧል

ባለፈው የውድድር ዘመን በኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ጠንካራ የነበረውን ቢሾፍቱ ከተማን የመራው አሰልጣኝ አስራት አባተ በይፋ የከፍተኛ ሊጉን ቡታጅራ ከተማን ተረክቧል ።

አሰልጣኝ አስራት አባተ በዘንድሮው የውድድር አመት በኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ በምድብ ሁለት ተደልድሎ የነበረውን ቢሾፍቱ ከተማን በዋና አሰልጣኝነት እየመራ ክለቡን በጠንካራ ጉዞ የምድቡ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ የአንደኛ ሊግ ማጠቃለያ በባቱ ከተማ በተከናወነው የመጨረሻ ወደ ከፍተኛ ሊግ ለመግባት በተደረገው መድረክ ክለቡን ማድረስ የቻለ ሲሆን ቢሾፍቱ ከተማን በመልቀቅ ወደ ቡታጅራ ከተማ መቀላቀል ችሏል።

ቡታጅራ ከተማ በተጠናቀቀው የውድድር አመት በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ በምድብ ሐ ተደልድሎ እስከመጫረሻ ላለመውረድ ሲታገል የነበረ ሲሆን በስተመጨረሻ ከወረጅ በእኩል ነጥብ በጎል ክፍያ ተሽሎ ከመውረድ የዳነ ሲሆን አዲሱ አሰልጣኝ አስራት አባተ በቀጣይ የክለቡን ጥንካሬ ለመመለስ በአዲሱ ክለባቸው ታምኖባቸዋል።

አሰልጣኝ አስራት አባተ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሴቶች ብሄራዊ ቡድን ፣የደደቢት የሴቶች ቡድን፣ አዲስ አበባ ከተማንና ቢሾፍቱ ከተማን በማሰልጠን ከፍተኛ ልምድ ያለው አሰልጣኝ ነው ።

www.AmharaSport.net

error: እባክዎትን ኮፒ ሲያደርጉ ምንጭ ይጥቀሱ!