የዋሊያዎቹ ይፋዊ አሰላለፍ ታውቋል

ለኳታር 2022 ዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ የመጀመርያ ጨዋታውን ከሌሶቶ ጋር ከቀናቶች በፊት በሜዳው ያለ ጎል በአቻ ውጤት የተለያየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በዛሬው ጨዋታ የሶስት ተጨዋቾች ለውጥ በማድረግ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ታውቋል ።

አሰልጣኝ አብረሃም መብራቱ በመጀመሪያው ጨዋታ ቋሚ ከነበሩ ተጨዋቾች መካከል ሙጂብ ቃሲም ፣ኡመድ ኡኩሪና ራማዳን የሱፍን በማሳረፍ በምትካቸው መስፍን ታፈሰ ፣ሀይደር ሸረፋ እና ደስታ ደሙን በቋሚ አሰላለፍ አካተው ወደ ሜዳ የሚገቡ ይሆናል ።

error: እባክዎትን ኮፒ ሲያደርጉ ምንጭ ይጥቀሱ!