ለዓለም ብርሃኑ ከዋልያዎቹ ስብስብ ውጪ ሆነ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የፊታችን ህዳር 6 አንታናናሪቮ ላይ ከማዳጋስካር እና ህዳር 9 መቐለ ላይ ከአይቮሪኮስት ጋር ላለበት 2021 የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዝግጅቱን ሰኞ ጥቅምት 24/2012ዓ.ም ማረፊያውን አክሱም ሆቴል መቐለ በማድረግ ይጀምራል።

የብሄራዊ ቡድኑ አባላትም እሁድ ጥቅምት 23/2012ዓ.ም በሸበሌ ሆቴል ከቀኑ 9 ሰዓት ሪፖርት በማድረግ ሰኞ ከረፋዱ 5ሰዓት ወደ መቐለ ያቀናሉ።

በመቐለ ቆይታቸው በቀን ሁለት ጊዜ ልምምድ የሚሰሩ ሲሆን ህዳር 1 ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ህዳር 2/2012ዓ.ም የቡድኑ አባላት ወደ ማዳጋስካር የሚያመሩ ይሆናል። ህዳር 6 ጨዋታቸውን በማዳጋስካር ካካሄዱ በኋላ በቀጣዩ ቀን ህዳር 7 ወደ አዲስ አበባ በመለስ፤ ህዳር 8 ወደ መቐለ በመሄድ ህዳር 9 ከቀኑ 10 ሰዓት ከአይቮርኮስት ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ የሆነው ለዓለም ብርሃኑ ከክለቡ ጋር በቅድመ ዝግጀት ልምምድ ላይ በደረሰበት ጉዳት ከዋልያዎቹ ስብስብ ውጭ መሆኑ ታውቋል። በምትኩ የመከላከያ እግር ኳስ ክለብ ግብ ጠባቂ አቤል ማሞ ጥሪ ተደርጎለታል ሲል የዘገበው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ነው።

error: እባክዎትን ኮፒ ሲያደርጉ ምንጭ ይጥቀሱ!