በእግር ኳሱ እየታየ ያለው ዘረኝነት ሊቀረፍ ይገባል ” የካፍ ፕሬዝዳንት”

በእግር ኳሱ እየታየ ያለው ዘረኝነት ሊቀረፍ እንደሚገባ የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዝዳንት አህመድ አህመድ አሳሰቡ ።

በእግር ኳሱ እየታየ ያለው ዘረኝነት ተቀባይነት እንደሌለውና ሊቀረፍ እንደሚገባው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አህመድ አህመድ አሳስበዋል፡፡

በአውሮፓ ሊጎች በቤልጂም፣ በጣሊያን ሴሪ ኣ አሁንም ድረስ ጥቁር ተጫዋቾች የዘረኝነት ሰለባ መሆናቸው በትዊተር ገፃቸው የገለፁት ፕሬዝዳንቱ ዘረኝት የእግር ኳሱ አካል አይደሉም፤ እንዲህ መሰል የዘረኝነትና ጅላጅልነት ተግባራት ከስፖርቱ መርህ ውጭ በመሆናቸው ሊወገዱ ይገባል ብለዋል፡፡

በእንደዚህ መሰል ድርጊቶች የሚሳተፉ አካላት ላይ ተገቢውን አስተማሪ ቅጣት ማስተላለፍ እንደሚገባም ነው ፕሬዝዳንቱ ያሳሰቡት፡፡

ምንጭ፡- አፍሪካን ኒውስ

© አማራ ስፖርት

error: እባክዎትን ኮፒ ሲያደርጉ ምንጭ ይጥቀሱ!