ኢትዮጵያን የሚገጥመው የኮትዲቫር ስብስብ ታውቋል

የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሃገር ኮትዲቯር አሰልጣኝ ኢብራሂም ካማራ ለካሜሮኑ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ኒጀርን እና ኢትዮጵያን የሚገጥመውን ቡድናቸውን ዝርዝር ዛሬ ከሰዓት በአቢዣን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ አድርገዋል ፡፡

ብሄራዊ ቡድኑ ኖቬምበር 16 አቢዣን ላይ የኒጀርን ብሔራዊ ቡድን ከገጠመ በኋላ ከሶስት ቀናት በኋላ ኖቬምበር 19 በትግራይ ዓለም ዓቀፍ ስታዲየም የኢትዮጵያ አቻውን ይገጥማል፡፡

ኢብራሂም ካማራ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንዳሉት ለግብጽ የአፍሪካ ዋንጫ የተካፈለውን ቡድን መነካካት ሳያስፈልጋቸው እንዳለ እንደሚመጡ ገልጸው ዋናው ምክንያታቸው በወጣቶች የተገነባና ኳስን በመቆጣጠር የሚጫወት ጥሩ ቡድን ማፍረስ እንደማያስፈልግ አሳውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያን የሚገጥመው የኮትዲቯር ብሔራዊ ቡድን ዝርዝር ይህን ይመስላል፡
ግብ ጠባቂዎች
1. ግቦሁ ሲልቨ (ቲፒ ማዜንቤ)
2. ባድራ አሊ ሳንጋሬ (ኡቶንጋቲ ኤፍ ሲ)
3. ሳዩባ ሞንዴ (ኦዴንስ ቦልድ ክለብ)
ተከላካዮች
4. ሴርዥ ኦርዬ (ቶተንሃም)
5. ብሪቶ ዊሊ (ዙሪክ ኤፍ ሲ)
6. ዢስለ ኮናን (ስታድ ድ ሬን)
7. ዎንሎ ኩሊባሊ (ቲፒ ማዜምቤ)
8. ኢስማኤል ትራኦሬ (ኦንዤ)
9. ዊልፍሬድ ካኖ (ፒራሚድ ኤፍ ሲ)
10. ሼክ ኮማራ (ዋይዳድ ካዛብላንካ)
11. ሲሞን ዴሊ (ክለብ ብሩዥ)

የመሃል ሜዳ ተጫዋቾች
12. ፍራንክ ኬሲ (ኤሲ ሚላን)
13. ሴኮ ፎፋና (ኡዲኔዝ)
14. ሃቢብ ማይጋ (ሜትዝ ኤፍ ሲ)
15. ኩኣሜ ኮፊ ክርስቲያን (ቲፒ ማዜምቤ)
16. ኢብራሂም ትራኦሬ (ስላቪያ ፕራግ)
17. ቪክቶሪያ ኦንግባን (ሜትዝ)
አጥቂዎች
18. ዊልፍሬድ ዛሃ (ክሪስታል ፓላስ)
19. ኒኮላ ፔፔ (አርሰናል)
20. ማክስ ግራዴል (ቱሉዝ)
21. ሮዤ አሳል (ያንግ ቦይስ)
22. ዮሃን ቦሊ (ሰን ትሮን)
23. ማክስዌል ኮርኔ (ኦሊምፒክ ሊዮኔ)
24. ያኩ ሜይት (ሬዲንግ)

Via – ሀትሪክ ስፖርት

አማራ ስፖርት

error: እባክዎትን ኮፒ ሲያደርጉ ምንጭ ይጥቀሱ!