የጅማ አባጅፋር ተጫዋቾች አድማ ሊያደርጉ ነው

ለበርካታ ወራቶች ደመወዝ ያልተከፈላቸው በቁጥር ስምንት ነባር የጅማ አባጅፋር ተጨዋቾች ያለ መጫዎት አድማ ሊያደርጉ መሆኑ ታውቋል ።

የተጨዋቾቹ የደመወዝ ይከፈለን ጥያቄ ለበርካታ ወራት የቆየና ፌዴሬሽኑም ክለቡ እንዲከፍል ቢወስንም እስካሁን ግን ተፈፃሚ ሳይሆን መቆየቱ ተጨዋቾቹ የመጨረሻ አማራጭ ያሉትን ውሳኔ ሊተገብሩ መስማማታቸውን አማራ ስፖርት መረጃውን ከተጨዋቾቹ አግኝቷል ።

በስድስት ክለቦች መካከል የሚካሄደው የአዳማ ከተማ ዋንጫ ነገ የሚጀምር ሲሆን ስምንቱ የጅማ አባጅፋር ተጫዋቾች እንደማይጫወቱ እና ያለመጫዎት አድማ እንደሚያደርጉ ለፌዴሬሽኑ በደብዳቤ ማሳወቃቸውንም ተጨዋቾቹ ነግረውናል ።

በአሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው የሚመራው አባጅፋር ነገ ከአዳማ ከተማ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ በቀሩት የቡድኑ ተጫዋቾች እንደሚጫዎት ይጠበቃል ።

©Amhara Sport

error: እባክዎትን ኮፒ ሲያደርጉ ምንጭ ይጥቀሱ!