የኢትዮጵያ እና አይቮሪኮስት ጨዋታ ባህር ዳር ላይ እንዲካሄድ  ተወስኗል

የኢትዮጵያ እና አይቮሪኮስት ጨዋታ ባህር ዳር ላይ እንዲካሄድ ተወስኗል

የኢትዮጵያ እና አይቮሪኮስት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የስታዲየም ለውጥ ተደርጎለት በግዙፉ በባህር ዳር አለምአቀፍ ስታዲየም እንዲካሄድ ተወስኗል ።

ከዚህ ቀደም የሁለቱ ሀገራት ጨዋታ በመቐለ ትግራይ ስታዲየም ሊካሄድ መርሐ ግብር ወጥቶለት እንደነበር የሚታወስ ሲሆን በትግራይ  ስታዲዬም ማካሄድ እንደማይችልና ጨዋታው በባሕር ዳር ስታዲዬም እንዲካሄድ ካፍ ወስኗል።

ካፍ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በደብዳቤ እንዳስታወቀው የትግራይ ስታዲዬም የካፍን ውድድሮች ለማካሄድ የወጣውን መስፈረት አያሟላም ብሏል። ።

በዚህ መሰረት ታህሳስ 9 የሚካሄደው ጨዋታ ከትግራይ ስቴድየም ወደ ባህርዳር ስታድየም ለውጥ ተደርጎበታል።

©AmharaSport

error: እባክዎትን ኮፒ ሲያደርጉ ምንጭ ይጥቀሱ!