ኢትዮጵያ በፊፋ የሃገራት ወርሃዊ ደረጃ አምስት ስፍራዎችን አሻሽላለች

ዓለም አቀፉ የእግርኳስ ማህበር ፊፋ በየወሩ ይፋ በሚያደርገው የፊፋ ኮካ ኮላ የሃገራት የእግርኳስ ደረጃ ቤልጂየም ፣ ፈረንሳይ እና ብራዚል ከአንድ እስከ ሶስት የተቀመጡበት በህዳር ወር ኢትዮጵያ 1061 ነጥብ ይዛ 146ኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥ ካለፈው ወር የአምስት ስፍራዎች መሻሻል አሳይታለች።

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በዚህ ወር ባደረጓቸው ሁለት የነጥብ ጨዋታዎች ላይ ዋሊያዎቹ በአንዱ ጨዋታ ተሸንፈው ከባዷን ኮት ዲቯርን በሜዳቸው የረቱበት ጨዋታ በወሩ ላሳዩት የደረጃ መሻሻልም ያስመዘገቡት ውጤት ምክንያት ሆኗል።

www.AmharaSport.net

error: እባክዎትን ኮፒ ሲያደርጉ ምንጭ ይጥቀሱ!