ድሬዳዋ ከነማ ለ37 ዓመታት የተጠቀመበትን ሎጎና ስያሜ ለውጥ አደረገ

የምስራቋ ድሬዳዋ ከተማ ወኪል የሆነው ድሬዳዋ ከነማ ለ37 ዓመታት ሲጠቀምበት የነበረውን የሎጎና ስያሜ ለውጥ አድርጓል ።

በ1975 ዓ/ም የተመሰረተው ድሬዳዋ ከነማ ቀደም ሲል ሲጠቀምበት የነበረውን የሎጎና ስያሜ ለውጥ ያደረገ ሲሆን ከዚህ ቀደም ድሬድዋ ከነማ እግርኳስ ክለብ የሚለው መጠሪያ “ድሬዳዋ ከተማ ስፖርት ክለብ ” ወደሚል ስያሜ ተቀይሯል ።

ከዚህ ቀደም ክለቡ የሚጠቀምበት የእግር ኳስ ምልክት ሎጎ በክለቡ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች የስፖርት አይነቶችን አለመወከሉ ለሎጎው መቀየር ዋነኛ ምክንያት መሆኑን ክለቡ አስታውቋል ።

በአዲሱ የክለቡ ሎጎ ድሬድዋ ከተማን ይገልፃሉ ተብለው የታመነባቸው ምልክቶች ያሉት ሲሆን ከነዚህም መካከል ባቡር ፣ ፀሀይ ፣እርግብ ፣አይቮሪ እና ጊር ይገኙበታል ።

ድሬድዋ ከተማ የሰላም ተምሳሌት ናት በሚል የሰላም እርግብ በሎጎ ላይ ሲካተት የከተማዋ አቅጣጫ በምስራቅ መሆኑ የፀሀይ ምልክት እንዳካተት ሁኗል ።

በሌላ በኩል የከተማዋን የቆዩ ቀደምት ታሪካዊ ህንፃዎች የሚገልፅ ምልክት ሲካተት አይቮሪው የከተማዋን የቀደሙ ክለቦች እነ ባቡር እና ጥጥ ማህበር የእግርኳስ ማህበሮችን የሚያስታውስ ውህድ ቀለም በመገለጫነት ተቀምጧል ።

የሎጎው መቀየር ክለቡ የድሬዳዋ ህዝብ ወኪል አምባሳደር በመሆን ሎጎው ድሬዳዋን መግለፅ እንዳለበት በመታመኑም ነው ተብሏል ።

ክለቡ ከዚህ በኋላ ስያሜውንም ከድሬዳዋ ከነማ ስፖርት ክለብ ወደ ድሬዳዋ ከተማ ስፖርት ክለብ መቀየሩንም አሳውቋል።

www.AmharaSport.net

error: እባክዎትን ኮፒ ሲያደርጉ ምንጭ ይጥቀሱ!