ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ | ስሑል ሽረ ከ ፋሲል ከነማ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 9ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ የሚደረጉ ሲሆን ዛሬ አርብ አንድ ጨዋታ የሚደረግ ይሆናል።

በዛሬው እለት ከሚደረጉት ጨዋታዎች መካከል ስሑል ሽሬ ከ ፋሲል ከነማ በ9 ሰአት በትግራይ ስታዲየም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

ሽረዎች በሜዳቸው ባሉ ጨዋታዎች ላይ
4 ተጫወቱ
1 አቻ
1 ተሸነፉ
2 አሸነፉ።

ስሑል ሽሬ በሊጉ ያለዉ መረጃ

ተጫወተ- 8
አሸነፈ- 3
ተሸነፈ -2
አቻ- 3
ልዩነት- -2
ነጥብ – 12
ደረጃ – 6

አጼዎቹ ከሜዳቸው ውጪ ባሉ ጨዋታዎች ላይ ብዙም ጥንካሬ እያሳዩ ባይሆንም በደረጃ ሰንጠረዡ በ15 ነጥብ ከተጋጣሚያቸው በ3 ነጥብ እርቀው 2ተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

አጼዎቹ ከሜዳቸው ውጪ ባሉ ጨዋታዎች ላይ
4 ተጫወቱ
3 አቻ
1 ተሸነፉ
0 አሸነፉ።

ፋሲል ከነማዎች በሊጉ ያላቸው መረጃ

ተጫወተ- 8
አሸነፈ- 4
ተሸነፈ – 1
አቻ- 3
ልዩነት- 11
ነጥብ – 15
ደረጃ – 2

ስሑል ሽረ በጉዳት ሆነ በቅጣት የሚያጡት ተጨዋች አይኖርም።

በፋሲል ከነማ በኩል ጉዳት ላይ የነበሩት ያሬድ እና እንየው ለዛሬው ጨዋታ አይደርሱም።

በሊጉ አስደናቂ ጊዜን እያሳለፈ የሚገኘው እና የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነቱን ደረጃ በ9 ጎሎች የሚመራው ሙጂብ ቃሲም ዛሬስ ጎል ማግባቱን ይቀጥልበት ይሆን? አብረን የምንመለከተው ይሆናል።

አጼዎቹ የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፉ ከሆነ የሊጉን መሪነት ከመቀለ 70 እንደርታ ይረከባሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ ስሁል ሽረዎች ድል የሚቀናቸው ከሆነ ደረጃቸውን ወደ 3ተኛ ከፍ ያደርጋሉ።

ጨዋታውን እንደተለመደው በተወዳጁ አማራ ስፖርት ድረ ገጽ እናስተላልፋለን።

error: እባክዎትን ኮፒ ሲያደርጉ ምንጭ ይጥቀሱ!