ባህርዳር ከተማ ከ ወልዋሎ አዲግራት ዩ. | ቅድመ ጨዋታ ዳሰሳ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 9ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ትላንት አርብ በተካሄደ አንድ ጨዋታ ሲጀመር ፋሲል ከነማ በመጨረሻ ደቂቃዎች ላይ በተቆጠሩበት 2 ጎሎች በ ስሁል ሽረ መሸነፉ አይዘነጋም።

ዛሬም ፕሪምየር ሊጉ ቀጥሎ ሲካሄድ 9:00 ሰአት ላይ በተለያዩ ስታዲየሞች ሰባት ጨዋታዎች የሚደረጉ ይሆናል።

በዛሬው እለት ከሚደረጉት ጨዋታዎች መካከል ባህርዳር ከተማ ከወልዋሎ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

የጣናው ሞገዶች በሜዳቸው እና በደጋፊዎቻቸው ፊት በሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ሽንፈት የሚባል ነገር አለመዱም።

በዚህ አመት እንኳን በሊጉ በሜዳቸው ካደረጓቸው 3 ጨዋታዎች ዉስጥ 3ቱንም ማሸነፍ ችለዋል።

የጣናው ሞገዶች በፕሪምየር ሊጉ ያላቸው መረጃ

ተጫወተ- 8
አሸነፈ- 3
ተሸነፈ -3
አቻ- 2
ልዩነት- -1
ነጥብ – 11
ደረጃ – 8

በባህርዳር ከነማ በኩል ጉዳት ላይ ያሉት አቤል እና ወሰኑ አሊ ለዛሬው ጨዋታ አይደርሱም።

በሊጉ አስደናቂ ጊዜን እያሳለፈ የሚገኘው እና የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነቱ ደረጃ ላይ በ6 ጎሎች በ2ተኛ ደረጃ የሚገኘው ፍፁም አለሙ ከጉዳት ተመልሶ በዛሬው ጨዋታ ቡድኑን የሚያገለግል ይሆናል።

በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ሰር ሆነው በሊጉ ጥሩ አጀማመር ያሳዩን ቢጫ ለባሾቹ ለባህር ዳር ከነማዎች ቀላል የማይባል ተፎካካሪ እንደሚሆኑም ይጠበቃል።

ቢጫ ለባሾቹ በፕሪምየር ሊጉ ያላቸው መረጃ

ተጫወተ- 8
አሸነፈ- 4
ተሸነፈ – 2
አቻ- 2
ልዩነት- 6
ነጥብ – 14
ደረጃ – 4

በወልዋሎ በኩል ጉዳት ላይ የሚገኙት አይናለም ሀይሉ እና ካርሎስ ዳምጠው ለዛሬው ጨዋታ አይደርሱም።

በሊጉ ሁለት ጊዜ እርስ በርስ የተገናኙት ሁለቱ ክለቦች ባህርዳር ላይ አቻ ሲወጡ ወለዋሎ በሜዳው የ 1-0 ድል ቀንቶታል።

ጨዋታውን እንደተለመደው በተወዳጁ አማራ ስፖርት ድረ ገጽ እናስተላልፋለን።

error: እባክዎትን ኮፒ ሲያደርጉ ምንጭ ይጥቀሱ!