የኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው ቅድመ ማጠሪያ ድልድሉ ላይ የሚከተለውን ሀሳብ ተናግረዋል
“የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አምኖብኝ ለብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት ጥሪ ሲያደርግልኝ ከፍተኛ ደስታ ነው የተሰማኝ ለእኔ ሀገርን ማገልገል መቻል ከምንም በላይ ነው። ስራው በተሰጠኝ ጊዜ አላማ አድርጌ የተነሳሁት ሀገሬን ለአፍሪካ ዋንጫ ማብቃት ነው። የአፍሪካ ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ከጅቡቲ ጋር መሆኑ እድለኛ ያደርገናል የሚሉ የስፖርት አፍቃሪያ አሉ ሀሳቡ ልክ ቢመስልም ይህ ማለት ጅቡቲ ተኝታ ትጠብቀናለች ማለት አይደለም። ፈረንሳያዊ አሰልጣኝ ቀጥረው እያሰሩ ይገኛሉ ይህም ምን ያህል እግር ኳሳቸውን ለማሳደግ እየሰሩ እንደሚገኝ ያሳያል። ሴካፋ ላይ የነበረኝ ቆይታን አስመልክቶ ሪፖርት አስገብቻለሁ በውድድሩ ደካማ እና ጠንካራ ጎናችንን ለይቻለሁ። አሰልጣኞች የተሻለ መስራት እንዲችሉ። ላለፉት 18 ዓመታት ላይ የሴቶች እግር ኳስ ላይ እንደመስራቴ መጠን ሀገራችንን ከፍ ለማድረግ እሰራሉ። ክለቦች ባልነበሩበት ጊዜ ለአፍሪካ ዋንጫ አልፈናል፤ አሁን ደግሞ ብዙ ነገሮች ከተጠቃማነት አንጻር በሴቶች እግር ኳስ በተስተካከሉ ጊዜ እና ክለቦች በበዙ ጊዜ ለማለፍ መቸገራችን ሁላችንንም ሊያሳስበን የሚገባ ጉዳይ ነው። ጠንክረን መስራት ይኖርብናል ”

Via EFF