የጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ | ፋሲል ከነማ ከ ሲዳማ ቡና

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ የሚደረጉ ሲሆን ዛሬ እሁድ አምስት ጨዋታዎች የሚደረጉ ይሆናል።

በዛሬው እለት ከሚደረጉት ጨዋታዎች መካከል ፋሲል ከነማ ሲዳማ ቡናን በሜዳው በ9 ሰአት የሚያስተናግድበትን ጨዋታ እንደሚከተለው ዳሰነዋል።

በሜዳቸው በሚደረጉ ጨዋታዎች ላይ ለተጋጣሚያቸው ነጥብ ላለመስጠት ማሸነፍ እና ማሸነፍ ብቻን አላማ አድርገው የሚገቡት አጼዎቹ ዛሬም የማሸነፉን ትልቅ ግምት ይይዛሉ።

አጼዎቹ በሜዳቸው ባሉ ጨዋታዎች ላይ
4 ተጫወቱ
0 አቻ
0 ተሸነፉ
4 አሸነፉ።

ፋሲል ከነማዎች በሊጉ ያላቸው መረጃ

ተጫወተ- 9
አሸነፈ- 4
ተሸነፈ -2
አቻ- 3
ልዩነት- 9
ነጥብ – 15
ደረጃ – 3

በፋሲል ከነማ በኩል ጉዳት ላይ የሚገኙ3 ያሬድ ባየህ እና እንየው ካሳሁን ለዛሬው ጨዋታ አይደርሱም።

ሲዳማ ቡናዎች ከሜዳቸው ውጪ ካደረጓቸው 5 ጨዋታዎች ውስጥ በሶስቱ ሽንፈትን ቢያስተናግዱም ባሏቸው ፈጣን አጥቂዎች በመታገዝ ለአፄዎቹ ፈታኝ እንደሚሆኑ እና በቀላሉም እጅ እንደማይሰጡ ይጠበቃል።

ሲዳማ ቡና ከሜዳቸው ውጪ ባሉ ጨዋታዎች ላይ
5 ተጫወቱ
0 አቻ
3 ተሸነፉ
2 አሸነፉ።

ሲዳማ ቡና በሊጉ ያላቸው መረጃ

ተጫወተ- 9
አሸነፈ- 4
ተሸነፈ – 5
አቻ- 0
ልዩነት- 2
ነጥብ – 12
ደረጃ – 10

ሲዳማ ቡናዎች በጉዳት ሚሊዮንን የማያሰልፉ ይሆናል።

አጼዎቹ የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፉ ከሆነ ነጥባቸውን ወደ 18 በማሳደግ ከመሪው መቀለ 70 እንደርታ በ 1 ነጥብ ዝቅ ብለው 2ተኛ ደረጃ ላይ የሚቀመጡ ይሆናል።

በሌላ በኩል ደግሞ ሲዳማ ቡናዎች ድል የሚቀናቸው ከሆነ ነጥባቸዉን ወደ 15 ከፍ ያደርጋሉ።

ጨዋታውን እንደተለመደው በተወዳጁ አማራ ስፖርት ድረ ገጽ እናስተላልፋለን።

www.amharasport.net

error: እባክዎትን ኮፒ ሲያደርጉ ምንጭ ይጥቀሱ!