የጨዋታ ቅድመ ዳሰሳ | ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ባህር ዳር ከተማ

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ የሚደረጉ ሲሆን ዛሬ እሁድ አምስት ጨዋታዎች የሚደረጉ ይሆናል።

በዛሬው እለት ከሚደረጉት ጨዋታዎች መካከል ባህር ዳር ከነማ ከሜዳው ዉጭ ተጉዞ ቅዱስ ጊዮርጊስን በ9 ሰአት የሚገጥምበትን ጨዋታ እንደሚከተለው ዳሰነዋል።

በዚህ የውድድር አመት ከሜዳቸው ውጭ በሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ላይ ማሸነፍ የተሳናቸው የጣናው ሞገዶች አሁን ደግሞ በተጨዋቾች እና በክለቡ መካከል ባለው የደሞዝ ክፈሉን ጉዳይ እሰጣ ገባ እየታመሱ ጨዋታቸውን ለማድረግ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የጣናው ሞገዶች በተጋጣሚዎቻቸው መረብ ላይ ጎሎችን ማግባት ላይ ጉድለት ባይታይባቸውም እስካሁን ከሜዳቸው ውጭ መሰብሰብ ከሚገባቸው 15 ነጥብ ውስጥ ማግኘት የቻሉት 2 ነጥብ ብቻ ነው።

ባህር ዳር ከነማ ከሜዳቸው ውጪ ባሉ ጨዋታዎች ላይ
5 ተጫወቱ
2 አቻ
3 ተሸነፉ
0 አሸነፉ።

ባህር ዳር ከነማዎች በሊጉ ያላቸው መረጃ

ተጫወተ- 9
አሸነፈ- 4
ተሸነፈ -3
አቻ- 2
ልዩነት- 0
ነጥብ – 14
ደረጃ – 6

በጣናው ሞገዶች በኩል ጉዳት ላይ የሚገኙት ወሰኑ አሊ እና አቤል ለዛሬው ጨዋታ አይደርሱም።

በዚህ የውድድር አመት የተጠበቁትን ያህል እየተጓዙ ያልሆኑት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ዛሬም በጉዳት የሚታመሰው ቡድናቸው ሳልሀዲንን፣ አቤል እና ናትናኤልን ሳይዝ ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል።

ፈረሰኞቹ በሜዳቸው ባሉ ጨዋታዎች ላይ

4 ተጫወቱ
1 አቻ
0 ተሸነፉ
3 አሸነፉ።

ፈረሰኞቹ በሊጉ ያላቸው መረጃ

ተጫወተ- 9
አሸነፈ- 3
ተሸነፈ – 1
አቻ- 5
ልዩነት- 2
ነጥብ – 14
ደረጃ – 5

ሁለቱ ቡድኖች ከዚህ በፊት 2 ግዜ የተገናኙ ሲሆን በሁለቱም ጨዋታዎች ላይ በጣና ሞገዶቹ የበላይነት ተጠናቋል።

በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ላይ በእኩል 14 ነጥብ በግብ ክፋያ ተበላልጠው እንደመገኘታቸው የዛሬውን ጨዋታ ተጠባቂ አድርጎታል።

የዛሬውን ጨዋታ የሚያሸንፈው ቡድን ነጥቡን ወደ 17 ያሳድጋል።

ጨዋታውን እንደተለመደው በተወዳጁ አማራ ስፖርት ድረ ገጽ እናስተላልፋለን።

www.amharasport.net

error: እባክዎትን ኮፒ ሲያደርጉ ምንጭ ይጥቀሱ!